am_tn/1sa/14/29.md

1.4 KiB

ለምድሪቱ

የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ለእስራኤል' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ዓይኔ በራ

በረታ የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እንደገና ብርታት አገኘ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ሕዝቡ ካገኙት … ምን ያህል የተሻለ

ሕዝቡ እንዲበላ ሊፈቀድለት ይገባ እንደነበር ለመግለጽ ዮናታን ይህንን በሁኔዎች ላይ የተደገፈ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ዐረፍተ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው የማረኩትን ዛሪ በነፃነት በልተው ቢሆን ኖሮ ድላችን የተሻለ ይሆን ነበር፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ተመልከት)

ምርኮ

ይህ ቃል ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ጋር በነበራቸው ጦርነት የወሰዷቸውን ነገሮች ያመለክታል፡፡

ስለዚህ አሁን ግድያው ታላቅ አልሆነም

በጦርነቱ ወቅቱ ወታደሮቹ ሊበሉ ስላልቻሉ፣ ቀኑ የረዘመውን ያህል እየደከሙ ሄዱ፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙ ፍልስጥኤማውያንን መግደል አልቻሉም፡፡