am_tn/1sa/14/24.md

1.2 KiB

ከወታደሮቹ ማንም ምግብ አልቀመሰም ነበር

ከሳኦል መሃላ የተነሣ ምንም መቅመስ እንዳልተፈቀደ ወታደሮቹ ተረድተው ነበር፡፡

ሕዝቡ ወደ ዱር ገባ

የፍልስጥኤም ወታደሮች ወደ ጫካ ሸሽተው ነበር የእስራኤል ወታደሮችም ወደዚያ ተከትለዋቸው ነበር፡፡

የሚፈስ ማር ነበር

በጫካ ውስጥ ምን ያህል ማር እንደነበር ለመግለጽ የተነገረ ግነት ነው፡፡ አት፡- "በሁሉ ሥፍራ በርካታ ማር ነበር' (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)

ማንም እጁን ወደ አፉ አልዘረጋም

በዚህ ስፍራ የአንድ ሰው እጁን በአፉ ማድረጉ መብላትን የሚያሳይ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ማንም ምንም አልበላም' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ሕዝቡ መሐላውን ፈርቶ

ሕዝቡ ይፈሩ የነበረው መሐላውን ሳይሆን መሐላውን ከመስበር ጋር የተያያዘውን ቅጣት ነበር፡፡ አት፡- "ሕዝቡ መሐላውን ከሰበሩ ሳኦል የሚያደርግባቸውን ፈሩ' (ምትክ ቃል ተመልከት)