am_tn/1sa/13/03.md

1.3 KiB

የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ

"የፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር'

ናሲብ

ይህ የፍልስጥኤም ጭፍራ የሰፈረበት የከተማ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)

ሳኦል እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ሁሉ ሰሙ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ዮናታን ለፈጸመው ጥቃት ሳኦል ኃላፊነቱን እየወሰደ ነበር ወይም 2) ዮናታን በፈጸመው ጥቃት የተገኘውን ድል ሳኦል እየወሰደ ነበር

እስራኤል ለፍልስጥኤም እንደ ብስባሽ ሽታ ሆነች

ፍልስጥኤማውያን ለእስራኤል ያላቸው ጥላቻ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን የሚረብሽ መጥፎ ሽታ እንደሆኑ ተደርጎ ተገለጾአል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ጠሉአቸው' (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)

ወታደሮቹ ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልጌላ ተሰበሰቡ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ሳኦል ወታደሮቹ እንዲከተሉት በጌልጌላ እንዲሰበሰቡ ጠራቸው (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)