am_tn/1sa/12/10.md

1.5 KiB

ወደ እግዚአብሔር ጮኹ

(እነርሱ) የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው

ይሩ ባአል

ይህ አንዳንዴ ይሩባአል በሚል ይተረጎማል፡፡ ይህ ሐሰተኛ አማልከትን ለመዋጋት የጻድቅ የክብርና የጥንካሬ ስም ነው፡፡

እግዚአብሔር ላከ … ድልም ሰጣችሁ

ሳሙኤል ከሕዝቡ የኃጢአት ኑዛዜና የእርዳታ ጥሪ በኋላ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገላቸው ታሪኩን ይናገራል፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ይሩ ባአል፣ ባርቅ፣ ዮፍታሔና ሳሙኤል

እነዚህ እግዚአብሔር ያስነሳቸወ ጥቂት የመሳፍንት ስሞች ናቸው፡፡ ሳሙኤል ራሱን በዚህ ዝርዝር ውስጥ አካቷል፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)

በአሊምንና አስታሮትን አገለገሉ

በዚህ ስፍራ ማገልገል ሐሰተኛ አማልክትን የማምለክን ተግባር ያመለክታል፡፡ አት፡- ሐሰተኛ አማልክትና ሴት አማልክትን አመለኩ (ምትክ ቃል ተመልከት)

የጠላቶቻችን እጅ

ይህ አረፍተ ነገር ኃይልን ለማመልከት "እጅ' የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ አት፡- "የጠላቶቻችን ኃይል ወይም የበላይነት' (ምትክ ቃል ተመልከት)