am_tn/1sa/12/03.md

1.6 KiB

በዚህ አለሁ፣በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ

በዚህ ንግግሩ ሳሙኤል አንዳች ተገቢ ያልሆነ ነገር በማንም ላይ አድርጎ ከሆነ ሕዝቡ እንዲናገር እየሞገተ ነው፡፡ አት፡- "አሁን በፊታችሁ ቆሜያለሁ፡፡ ምንም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ ነገር አድርጌ ከሆነ በእግዚአብሔርና በቀባው በንጉሡ ፊት እንድትናገሩ እጠይቃችኋለሁ፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ?

እንሰሳቶቻቸውን ያልሰረቀባቸውን ሰዎች ለማሳሳብ ሳሙኤል አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እኔ ውድ የሆነ እንስሳ ፈጽሞ ከማንም አልሰረቅሁም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ማንንስ ሸነገልሁ

ሁልጊዜ ታማኝ እንደ ነበር ለመናገር ሳሙኤል ሌላ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እኔ ማንንም አልታለልኩም ወይም ከማንም ጉቦ አልተቀበልሁም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

መስክሩብኝ እኔም እመለሳለሁ

"ከእነዚህ ክፉ ነገሮች ማናቸውንም አድርጌ ከሆንሁ አሁን ተናገሩ፣ የወሰድኩትንም እመለሳለሁ፡፡ ማናኛውንም ስሕተት አስተካክላለሁ፡፡'