am_tn/1sa/11/06.md

1.4 KiB

የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት

ወረደበት የሚለው ቃል የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ላይ ተጽእኖ ያድርጋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሣቸው ሕዝቡ በፍርሃት እንዲያከብሩትና ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ እንዲያደርግ ሳኦልን አስችሎታል፡፡ 1ሳሙኤል 10፡6ን እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ተከትሎ የማይወጣ

ናዖስንና አሞናውያንን ለመወጋት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲመጡ ሳዖል ጥሪ እያስተላለፈ ነበር፡፡

ከዚያም የእግዚአብሔር ድንጋጤ በሕዝቡ ላይ ወደቀ

እንደ ንጉሣቸው ሳኦልን በፍርሃት እንዲያከብሩት እግዚአብሔር ሕዘቡን አስቻለ፡፡ በውጤቱም ሰዎቹ ከሳኦል ጋር በቤዜቅ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡

ቤዜቅ

ይህ በኢያቢስ ገለዓድ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)

የእስራኤል ሰዎች ሦሥት መቶ ሺህ፣ የይሁዳም ሰዎች ሠላሣ ሺህ ነበሩ

"የእስራኤል ሰዎች 300,000፣ የይሁዳም ሰዎች 30,000 ነበሩ' (ቁጥሮች ተመልከት)