am_tn/1sa/09/15.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ጸሐፊው ታሪኩን መናገር ያቆምና አንባቢው በመቀጠል የሚሆነውን እንዲረዳ የታሪካዊ ዳራ መረጃ ይሰጣል፡፡ (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ተመልከት)

ልዑል ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ

በዚህ ስፍራ ልዑል የሚለው ቃል ንጉሥ በሚለው ፈንታ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር የመረጠው ሰው ይህ ነው፡፡ (የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም ተመልከት)

የብንያም ምድር

"ከብንያም ነገድ የሆኑ ሰዎች የሚኖሩበት ምድር'

ከፍልስጥኤማውያን እጅ

በዚህ ስፍራ እጅ የሚለው ቃል ቁጥጥር ለሚለው ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር' ወይም "ከእንግዲህ ወዲያ ፍልስጥኤማውያን አይቆጣጠሩአቸውም'

ሕዝቤን በሐዘኔታ ተመልክቼአለሁና

"ሕዝቤ መከራ እያዩ ናቸው እኔም ልረዳቸው እፈልጋለሁ'