am_tn/1sa/06/19.md

2.0 KiB

ወደ ታቦቱ ውስጥ ተመልክተዋል

ታቦቱ እጅግ ቅዱስ ስለ ነበር ማንም ወደ ውስጥ እንዲመለከት አልተፈቀደለትም፡፡ ታቦቱን እንኳን ለማየት የተፈቀደላቸው ካህናት ብቻ ናቸው፡፡

50,070 ሰዎች

"አምሳ ሺህ እና ሰባ ሰዎች' (ቁጥሮች ተመልከት)

በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ማን ይችላል?

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) ሕዝቡ ስለ እግዚብሔር ያደረበትን ፍርሃት ለመግለጽ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ አት፡- "ቅዱስ ስለሆነ እግዚአብሔርን መቋቋም የሚችል ማንም የለም!' ወይም 2) መረጃ ለማግኘት የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚለው ሐረግ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትን የሚያመለክት ነው፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሔር ታቦቱን እንዲይዝ የፈቀደለትን ካህን እፈለገ መሆኑን ያመላክታል፡፡ አት፡- "በመካከላችን ይህን ቅዱስ አምላክ፣ ያህዌን ማገልገልና ታቦቱን ማስተዳደር የሚችል ካህን አለን?' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎችንና እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ታቦቱ ከእኛ ወደ ማን ይሄዳል?

መረጃ ለማግኘት የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡ ሁለተኛ እንዳይቀጣቸው እግዚአብሔርና ታቦቱ ወደ አንድ ቦታ እንዲሄዱ ሕዝቡ እንደፈለገ ይጠቁማል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ሁለተኛ እንዳይቀጣን ይህን ታቦት ወዴት መስደድ እንችላለን?' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)