am_tn/1sa/06/10.md

1.2 KiB

ሁለት የሚያጠቡ ላሞች

እስከ አሁን ወተት የሚጠጡ ጥጆች ያሉአቸው ሁለት ላሞች፡፡ 1ሳሙኤል 6፡7ን እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

አይጦች

ይህን በ1ሳሙኤል 6፡4 እንዳለው ተርጉም፡፡

የእባጮቻቸውን ቅርጾች

"የእባጮቻቸውን ምሳሌዎች'

እጢ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡

ላሞቹ ወደ ቤትሳሚስ አቅጣጫ አቅንተው ሄዱ

በአብዛኛው የሚያጠቡ ላሞች ወደ ጥጆቻቸው ይመለሳሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ላሞች ወደ ቤትሳሚስ ሄዱ፡፡

እምቧ እያሉ ሄዱ

እምቧ ማለት ላሞች በድምጻቸው የሚፈጥሩት ጩኸት ነው፡፡

ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም

"ከአውራ ጎዳናው አልወጡም፡፡' ይህ በአዎንታ እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "በአውራው ጎዳና ዘለቁ' ወይም "ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር'