am_tn/1sa/06/05.md

2.4 KiB

ምሳሌዎች

ምሳሌ እውነተኛው ነገር የሚመስል ነገር ነው፡፡

እጢ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡

የሚያወድሙ

"የሚያጠፉ'

የእስራኤል አምላክ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

እጁን ከእናንተና ከአማልክቶቻችሁ፣ ከምድራችሁም ያነሳል

በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል እግዚአብሔር መከራን ለማምጣትና ለመቅጣት ያለውን ኃይል ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "እናንተን፣ አማልክቶቻችሁንና ምድራችሁን መቅጣት ያቆማል' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳደነደኑ ልባችሁን ለምን ታደነድናላችሁ?

ካህናቱና ጠንቋዮቹ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በመጠቀም፣ እግዚአብሔርን መታዘዝ እምቢ ካሉ ምን ሊሆን እንደሚችል ትኩረት ሰጥተው እንዲያስቡ ፍልስጥኤማውያንን አጥብቀው እያስገነዘቡ ነው፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ልባችሁን ታደነድናላችሁ

ይህ ግትር መሆንና ለእግዚብሔር ፈቃድ አለመታዘዝ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ግብጻውያን ሕዝቡን አልሰደዱአቸውምን እነርሱም አልሄዱምን?

ይህ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ መከራ ማምጣቱን እንዲያቆም በስተመጨረሻ ግብጻውያን እንዴት እስራኤላውያን ከግብጽ እንዲወጡ እንዳደረጉ ፍልስጥኤማውያንን ለማሳሳብ የተጠቀሙበት አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)