am_tn/1sa/02/29.md

2.0 KiB

አያያዥ አሳብ

የእግዚአብሔር ሰው ለዔል መናገሩን ቀጠለ

በማደሪያዬ … መሥዋዕቴን ስለምን ናቃችሁ?

ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ የሚገሥጽ ነው፡፡ በገላጭ አባባልነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት "በማደሪያዬ … መሥዋዕቴን ልትንቁ አይገባችሁም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ማደሪያዬን

"ሕዝቤ ቁርባን ለእኔ የሚያቀርቡበት ቦታ'

ከእያንዳንዱ ቁርባን በተሻለው ራሳችሁን ለማወፈር

ከቁርባኑ የተሻለው ክፍል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሆኖ መቃጠል ነበረበት፣ ካህናቱ ግን፡ ይበሉት ነበር፡፡

የአባትህ ቤት

"ቤት' የሚለው ስም በቤቱ ውስጥ ላሉ ሰዎች ምትክ ስም ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 2፡27 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አት ፡- "የአባትህ ቤተሰብ' (ምትክ ስም ተመልከት)

በፊቴ ልትሄድ ይገባሃል

ይህ "ለእኔ በመታዘዝ ኑር' የሚል ትርጉም ያለው ዘይቤአዊ አነጋገር ነው፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)

ይህን ማድረግ ከእኔ ይራቅ

"በእርግጥ ቤተሰብህ እኔን ለዘላለም እንዲያገለግለኝ አልፈቅድም'

የናቁኝ በጥቂቱ ይከብራሉ

"በጥቂቱ ይከበራሉ' የሚሉት ቃላት "እጅግ ይዋረዳሉ' ለሚለው የማያስደስት ቃል በምጸት የተተካ ቃል ነው፡፡ ይህ በአድራጊ አንቀጽ እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የሚንቁኝን በጥቂቱ አከብራለሁ' ወይም "የሚንቁኝን በእጅጉ አዋርዳለሁ' (ምጸት፣የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)