am_tn/1sa/02/03.md

1.9 KiB

አያያዥ አሳብ

ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ ሌሎች ሰዎች እየሰሟት እንዳሉ አድርጋ ትናገራለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)

አትታበዩ

"በትዕቢት አትናገሩ'

ሥራዎች በእርሱ ይመዘናሉ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት እርሱ የሰዎችን ሥራዎች ይመዝናል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን ለምን እንደሚያደርጉ ያውቃል (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሮአል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡፡ 1) ቀስቶቹ ራሳቸው ተሰብረዋል ወይም 2) ቀስት የያዙ ሰዎች ከማድረግ ተከለከሉ፡፡ አት፡- "ኃያላን ቀስተኞች ሰዎች ከማድረግ ተከለከሉ'

የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሮአል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር የኃያላን ሰዎችን ቀስት ይሰብራል' ወይም "እግዚአብሔር ኃያላን ሰዎችን እንኳን ደካሞች ያደርጋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ደካሞች (የሚሰናከሉ) እንደ መታጠቂያ ኃይልን ታጥቀዋል

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ከእንግዲህ ወዲህ አይሰናከሉም ነገር ግን ኃይላቸው እንደ መታጠቂያ ጠብቆ አብሯቸው ይኖራል ማለት ነው፡፡ አት፡- "የሚሰናከሉትን ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (˜ይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

መታጠቂያ … ታጥቀዋል

ይህ ለሥራ ለመዘጋጀት አንድን ነገር በወገብ ዙሪያ ስለማሰረ ጥቅም ላይ የሚውል አጠቃላይ ቃል ነው፡፡