am_tn/1sa/01/15.md

1.9 KiB

እኔስ ልባዋ ያዘነባት ሴት ነኝ

"እኔ እጅግ ያዘንኩ ሴት ነኝ፡፡'

በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ

ይህ "ጥልቅ የሆነ ስሜቴን ለእግዚአብሔር እየነገርኩ ነኝ' የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ባሪያህን እንደ … አትቁጠር

ሐና ትህትናዋን ለማሳየት ስለ ራሷ በሁለተኛ መደብ ተውላጠ ስም ትናገራለች፡፡ በአንደኛ መደብ ተውላጠ ስም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ባርያህን እንደ … አትቁጠረኝ' ወይም "አትቁጠረኝ' (አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

ከጭንቀቴና ከብስጭቴ ብዛት እስከ አሁን ተናግሬአለሁ

እንደ 1፡15፣ ሐዘንተኛ ልብ እንዳላት የተነገረ ሌላ የአባባል መንገድ ነው፡፡ ብዛት፣ ጭንቀት እና ብስጭት የሚሉት የነገር ስሞች በቅጽልነት እና በማሰሪያ አንቀጽነት ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አት፡- "እስካሁን የተናገርኩት በጣም ስላዘንኩና ተፎካካሪዬ እጅግ ስላበሳጨችኝ ነው፡፡' (የነገር ስም ተመልከት)

ጭንቀትና ብስጭት

እነዚህ ሁለቱም ቃላት ተፎካካሪዋ ታበሳጫት ስለነበር ሐና ታዝንና ትናደድ ነበር የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)

ጭንቀት

ፍናና ታስቆጣትና ታናድዳት ነበር፡፡

ብስጭት

ፍናና ክፉ ስለሆነችባት ሐና ይሰማት የነበረውን የሐዘንና የውርደት ስሜት እያመለከተች ነው፡፡