am_tn/1sa/01/07.md

1.2 KiB

ተፎካካሪዋ

የሕልቃና ሌላኛዋ ሚስት ፍናና ነች፡፡ ተፎካካሪ ማለት ሌላውን ሰው በመቃወም የሚወዳዳር ሰው ማለት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ሕልቃና አብልጦ እንዲወዳት ፍናና ሐናን በመቃወም ትወዳደራት ነበር፡፡

ሐና ሆይ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሽም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን?

አስፈላጊ ከሆነ አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች በገላጭ አባባል ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አት፡- "ሐና ማልቀስ የለብሽም፡፡ እኔ ለአንቺ ከአሥር ልጆች ይልቅ ስለምሻልሽ ልትበይና ልብሽም ደስ ሊለው ይገባል፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)

ከአስር ልጆች ይልቅ

ሐና ምን ያህል ለእርሱ አስፈላጊ እንደሆነች አጽንዖት ለመስጠት ሕልቃና አጋኖ እየተናገረ ነው፡፡ አት፡- "ማንኛውም ልጅ ሊሆነው ከሚችለው በላይ' (ግነትና ማጠቃለያ ተመልከት)