am_tn/1ki/22/51.md

1.6 KiB

ለሁለት አመታት ነገሠ

"ለ2 አመታተት ገዛ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

በያህዌ እይታ ክፉ የሆነውን

የያህዌ እይታ የሚነገረው ያህዌ ያንን ነገር እንዳየው ተደርጎ ነው፡፡ "ያህዌ ክፉ ብሎ የሚቆጥረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአባቱ መንገድ ሄደ፣ በእናቱ መንገድ ሄደ፣ በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ

የአንድ ሰው ባሕሪይ የሚገለጸው ያ ሰው በመንገድ ላይ እየሄደ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "አባቱ፣ እናቱ፣ እና የናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም ያደረጉትን ተመሳሳይ ነገር አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እስራኤልን ወደ ኃጢአት መራ

እዚህ ስፍራ "እስራኤል" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት የመረቱትን አስሩን ሰሜናዊ ነገዶች ነው፡፡

እርሱ በዓልን አገለገለ፣ ደግሞም አመለከው

"አገለገለ" እና "አመለከ" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል አምላክ

እዚህ ስፍራ "እስራኤል" የሚለው ቃል የሚያመለክተው መላውን አስራ ሁለቱን የያዕቆብ ትውልድ ነገዶች ነው፡፡