am_tn/1ki/22/39.md

1.5 KiB

በእስራኤል ነገሥታት ስራዎች መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው የሚገኙ አይደለምን?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፤ ደግሞም መልሱ አዎንታዊ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ጥያቄው ቃለ ምልልሳዊ ሲሆን ያገለገለውም ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 15፡31 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እነዚህ ታሪኮች የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች በተጻፉባቸው መጽሐፍት ውስጥ ተጽፈዋል፡፡" ወይም "በእስራኤል ንጉሦች ተግባራት መጽሐፍት ውስጥ ልታነቧቸው ትችላላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ/ተኛ

የአክዓብ መሞት የተገለጸው እንደተኛ ተደርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ መተኛት ሞትን የሚወክል ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 2፡10 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ)