am_tn/1ki/22/24.md

1.1 KiB

የያህዌ መንፈስ አንተን የተናገረው፣ እኔን በየት መንገድ አልፎ ነው?

ሰዴቅያስ ይህንን ምጸታዊ ጥያቄ የጠየቀው ሚክያስን ለመስደብ እና ለመገሰጽ ነው፡፡ "የያህዌ መንፈስ እኔን አልፎ አንተን የሚናገርህ አይምሰልህ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

"አድምጥ" ወይም "ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ"

አንተ ታያለህ

"ለጥያቄህ መልሱን ታውቃለህ፡፡" የሴዴቅያስ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ቢተረጎም፣ ይህ ሀረግ በስውር ያለውን መረጃ ለማቅረብ ይተረጎማል፡፡ "የያህዌ መንፈስ ለእኔ እንደተናገረ ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)