am_tn/1ki/22/18.md

1.2 KiB

አልነገርኩህምን … እርሱ ጥፋት ብቻ?

አክዓብ ይህንን ጥያቄ ያነሳው ስለ ሚክያስ የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ጥፋትን ብቻ እንደሚናገር…አልነገርኩህም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በሬማት ገለዓድ ይወድቃል

የአክዓብ በጦርነት ውስጥ መሞት የተገለጸው እንደሚወድቅ ተደርጎ ነው፡፡ "በሬማት ገለዓድ ይሞታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ)

ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ…ደግሞም ሌላው እንዲህ አለ

"አንዱ…ደግሞም ሌላው" የሚለው የሚያመለክተው በቀደመው ቁጥር ለቀረበው ለያህዌ ጥያቄ ከሰማያት ጭፍሮች ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መላዕክት የሚሰጡትን ምላሽ ነው፡፡