am_tn/1ki/22/03.md

1.8 KiB

ሬማት ገለዓድ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁን፣ ነገር ግን እኛ ከአራም እጅ እርሷን ለመውሰድ ምንም እያደረግን አይደለም?

አክዓብ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው እስከ አሁን ሬማት ገለዓድን መልሰው መያዝ እንደመበረባቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ሬማት ገለዓድ የእኛ ናት፣ ነገር ግን እኛ ከአራም ንጉሥ መልሰን ልንወስዳት ምንም ነገር አላደረግንም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከአራም ንጉሥ መልሰን ልንወስዳት

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል ሀይልን ያመለክታል፡፡ "ከአራም ንጉሥ ቁጥጥር ስር ነጻ ልናወጣት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ያው እንደ አንተው ነኝ፣ የእኔ ህዝብ እንዳንተ ህዝብ ነው፣ ደግሞም የእኔ ፈረሶች የአንተ ፈረሶች ናቸው

ኢዮሳፍጥ ለአክዓብ፣ የእርሱ ሰዎች እና የእርሱ ፈረሶች የአክዓብም መሆናቸውን ይነግረዋል፤ ይህም ማለት አክዓብ ደስ እንዳሰኘው ሊያዝባቸው ይቻላል ማለት ነው፡፡ "እኔ፣ የእኔ ወታደሮች፣ እንደዚሁም ፈረሶቼ አንተ በወደድከው መንገድ ልትተቀምባቸው የምትችላቸው የአንተም ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)