am_tn/1ki/20/13.md

2.0 KiB

ከዚያ እነሆ

"እነሆ" የሚለው በታሪኩ ውስጥ አዲስ ሰው በድንገት ብቅ እንደሚል ያነቃናል፡፡ የእናንተ ቋንቋ ይህን የሚገልጽበት መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡

ይህን ታላቅ ሰራዊት አያችሁን?

ያህዌ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው የቤን ሀዳድን ሰራዊት መጠን እና ጥንካሬ አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ይህንን ታላቅ ሰራዊት ተመልከቱ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ፣ ዛሬ በእጃችሁ ላይ እጥለዋለሁ/አደርገዋለሁ

"እነሆ" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚሆነው አስደናቂ መረጃ ትኩረት እንደንሰጥ ያነቃናል፡፡

በእጃችሁ ላይ አደርገዋለሁ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል ሀይልን ያመለክታል፡፡ "በዚያ ሰራዊት ላይ ድል እሰጣችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በማን?

አክዓብ ‘ይህን ታደርጋለህን' የሚለውን ቃል ትቶታል፡፡ "ይህን በማን ታደርጋለህ?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኢሊፕሲስ/የተተወ ወይም የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

አክዓብ ወጣት መኮንኖችን ጠራ

"አክዓብ ወጣት መኮንኖችን ሰበሰበ"

ሁሉም ወታደሮች፣ መላው የእስራኤል ሰራዊት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ተጣምረው የቀረቡት ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰባት ሺህ

"7,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)