am_tn/1ki/19/09.md

1.4 KiB

በዚያ በሚገኝ ዋሻ

እዚህ ስፍራ "እዚያ" የሚለው ቃል የኬብሮንን ተራራ ያመለክታል፡፡ ዋሻ በተራራ አጠገብ የሚገኝ ወደ ተፈጥሮ ክፍሎች ወይም ከመሬት በታች ወደሚገኝ ክፍል የሚመራ ክፍት ስፍራ ነው፡፡

የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፣ "ምን

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር የዋለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 6፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ለእርሱ መልዕክት ሰጠው" እንዲህም አለው፣ 'ምን" ወይም "ያህዌ ለእርሱ ይህ መልዕክት ሰጠው፡ 'ምን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኤልያስ ሆይ፣ እዚህ ምን ታደርጋለህ?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ኤልያስን ለመገሰጽ እና ግዴታውን ሊያስታውሰው ነው፡፡ "ኤልያስ ሆይ፣ መገኘት ያለብህ እዚህ ስፍራ አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ብቻ፣ ብቻዬን ቀረሁ

"እኔ" የሚለው ቃል የተደጋገመው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡