am_tn/1ki/18/27.md

2.4 KiB

ምናልባት በሀሳብ ላይ ይሆናል

"ምናልባት እያሰበ ይሆናል" ወይም "በሃሳብ ላይ ሆኖ ሊሆን ይችላል"

ራሱን ከህመም እያስታገሰ

ይህ ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ከባድ የሆነውን ሀሳብ ሻል ባለ መንገድ መግለጫ ነው፡፡ ኤልያስ በበዓል ላይ ያለውን ንቀት በፌዝ ይገልጻል፡፡ "በመታጠቢያ ቤት ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ)

ሊቀሰቀስ ያስፈልገዋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ልትቀሰቅሱት ያስፈልጋችኋል" ወይም "ከተኛበት ልታነቁት ይገባችኋል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አሁንም ይረበሹ ነበር

"እንስሳዊ ባህሪያቸውን ማሳየታቸውን ቀጥለዋል፡፡" ነቢያቱ ብዙውን ጊዜ ያልተለመደ መንገድ ወይም ጤናማ ያልሆነ ድርጊት ይፈጽሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ሲጨፍሩ በዓልን ጮኸው ይጣሩ፣ እና ራሳቸውን በስለት ይቆርጡ ነበር፡፡

የምሽት መስዋዕት ሲያቀርቡ

"የምሽት መስዋዕት ማቅረብ"

ነገር ግን ድምጽ አልነበረም ወይም ማንም የሚመልስ አልነበረም፤ ለልመናቸው አንዳች ትኩረት የሚሰጥ አልነበረም

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ደግሞም ለሀሰተኛ ነቢያት ጸሎት ምላሽ የሚሰጥ አለመኖሩን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "ነገር ግን በዓል አንዳች ነገር አልተናገረም ወይም አላደረገም ወይም ትኩረት እንኳን ሊሰጣቸው አልቻለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ድምጽ አልነበረም ወይም መልስ የሚሰጥ ማንም አልነበረም

ይህ በ1 ነገሥት 18፡26 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡