am_tn/1ki/18/09.md

2.1 KiB

እርሱ ይገድለኝ ዘንድ … እኔ ምን በድያለሁ?

አብድዩ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ንጉሥ አክአብ በኤልያስ ላይ ባለው ቁጣ ምክንያት እርሱ የሚደርስበትን አደጋ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እርሱ ይገድለኝ ዘንድ…እኔ በአንተ ላይ ስሀተት አልፈጸምኩም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋይህን ለአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጥ ዘንድ

"እጅ" ለሃይል እና ቁጥጥር ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "አገልጋይህን ለአክዓብ አሳልፈህ ለመስጠት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ አገልጋይ

አብድዩ ኤልያስን ለማክበር ራሱን የኤልያስ አገልጋይ ሲል ይናገራል፡፡

በህያው አምላክህ እምላለሁ

ይህ መሃላ የሚያገለግለው እርሱ እየተናገረ ያለው ነገር እውነት መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡

ጌታዬ ሰዎችን ያላከበት አገር ወይም ግዛት የለም

እዚህ ስፍራ "አገር ወይም ግዛት የለም" የሚለው ሰዎች ኤልያስን ፍለጋ በጣም ሩቅ ስፍራ ድረስ መሄዳቸውን በማጋነን የዋለ አገላለጽነው፡፡ ይህ በአዎንታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጌታዬ ሰዎችን ወደ እርብ እና ሩቅ አገራት እና ግዛቶች ልኳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት እንደዚሁም ጥንድ አሉታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

አሁን ግን

ይህ ሀረግ የዋለው ኤልያስ፣ አብድዩ ያደርገው ዘንድ የነገረው ነገር አደገኛ መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡