am_tn/1ki/18/01.md

979 B

የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር የዋለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 6፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ የእርሱን መልዕክት ተናገረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በምድሪቱ ላይ ዝናብ ላከ

"በምድሪቱ ላይ እንዲዘንብ አደረገ"

አሁን ችጋሩ/ረሃቡ ታላቅ ነበር

"አሁን" የሚለው ቃል እዚህ ስፍራ የዋለው በዋናው የታሪክ አካሄድ ላይ ማረፊያ ለማበጀት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው ድርቁ/ችጋሩ ምን ያህል ሰማርያን እንደጎዳት የመረጃ ዳራ ይሰጠናል፡፡ (የመረጃ ዳራ/መነሻ የሚለውን ይመልከቱ)