am_tn/1ki/17/19.md

1.8 KiB

እርሱ በነበረበት ስፍራ

እዚህ ቦታ "እርሱ" የሚለው የሚያመለክተው ኤልያስን ነው፡፡

በገዛ ራሱ አልጋ ላይ

እዚህ ቦታ "የእርሱ" የሚለው የሚያመለክተው ኤልያስን ነው፡፡

አንተም ደግሞ ተቀብላ የምታስተናግደኝ መበለት ላይ ልጇን በመግደል ጥፋትን ታመጣባታለህን?

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኤልያስ በእውነት ጥያቄ እየጠየቀ ነው፡፡ "ተቀብላ የምታስተናግደኝን መበለት፣ ልጇን በመግደል ለምን ብዙ እንድትሰቃይ ታደርጋለህ" ወይም 2) ኤልያስ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ምን ያህል እንዳዘነ ለመግለጽ ነው፡፡ "በእርግጥ፣ ተቀብላ የምታስተናግደኝን መበለት ልጇን በመግደል ይበልጥ እንድተሰቃይ አታደርግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተም በመበለቲቱ ላይ ጥፋት ታመጣለህ

መበለቲቱ መሰቃየቷ የተገለጸው "ጥፋት" እንደ ዕቃ በእርሷ ላይ የተቀመጠ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ደግሞ ጥፋት ታመጣባታለህ

እዚህ ስፍራ "ደግሞ/በተጨማሪ" የሚለው ትርጉም ድርቅ ካደረሰባት ጥፋት በተጨማሪ ማለት ነው፡፡

ራሱን በትንሹ ልጅ ላይ ዘረጋ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "በትንሹ ልጅ ላይ ተጋደመ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)