am_tn/1ki/15/33.md

1.8 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ይህ ምዕራፍ በ1 ነገሥት 15፡27-28 ባለው ክፍል ባኦስ እንዴት እንደነገሠ ይናገራል፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ባኦስ እንዴት የእስራኤል ንጉሥ መሆን እንደጀመረ መናገር ይጀምራሉ፡፡

ቴርሳ

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ ይህ በ1 ነገሥት 14፡17 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በያህዌ እይታ ክፉ የሆነውን

የያህዌ እይታ የሚለው የሚወክለው የያህዌን ፍርድ ነው፡፡ "በያህዌ ፍርድ/ሚዛን ክፉ የሆነውን" ወይም "ያህዌ ክፉ ብሎ የሚቆጥረውን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በኢዮርብዓም መንገድ ሄደ

እዚህ ስፍራ መሄድ የሚወክለው ድርጊትን ነው፡፡ "ኢዮርብዓም ያደረገውን ተመሳሳይ ነገር አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ኃጢአት እስራኤልን ወደ በደል በመራበት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች "የእርሱ" እና "እርሱ" የሚያመለክቱት 1)በኦስን ወይም 2)ኢዮርብዓምን ነው፡፡

እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራቱ

ሰዎችን አንድ ነገር እንዲያደርጉ መምራት የሚገልጸው አንድ ነገር እንዲፈጸሙ ተጽዕኖ ማሳደርን ነው፡፡ "እስራኤል ኃጢአት እንዲያደርግ ተጽዕኖ በማሳደሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)