am_tn/1ki/15/29.md

2.3 KiB

ባኦስ የኢዮርብዓምን ቤተሰብ በሙሉ ገደለ፡፡ አንድም የኢዮርብዓምን ትውልድ እስትንፋስ አላስቀረም፡፡

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የተጣመሩት ትውልዶቹ መገደላቸውን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መላው የኢዮርብዓም ቤተሰብ

ኢዮርብዓም የንጉሥ ናዳብ አባት ነበር፡፡

ከኢዮርብዓም ቤተሰብ አንድም በእስትንፋስ አላስቀረም

እስትንፋስ የሚወክለው በህይወት መትረፍን ነው፡፡ "ከኢዮርብዓም ቤተሰብ አንዱንም በህይወት አላስቀረም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ የንግሥና መስር

"የኢዮርብዓም የንግሥና መስመር/ዘር ሀረግ"

ያህዌ ልክ በአገልጋዩ በሴሎናዊው በአኪያ እንደተናገረው

በ1 ነገሥት 14፡10-11 ላይ ያህዌ በነቢዩ አኪያ በኩል ቤተሰቡን እንደሚያጠፋ ለኢዮርብዓም ተናግሮታል፡፡

ሴሎናዊው አኪያ

"ከሴሎና የሆነው፣ አኪያ"

ኢዮርብዓም ለፈጸማቸው ኃጢአቶች እና እስራኤልን ወደ ኃጢአት ለመምራቱ

"ኃጢአት" የሚለው ረቂቅ ስም በግሥ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ኢዮርብዓም ኃጢአት በመፈጸሙ ምክንያት እና በተመሳሳይ መንገድ እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራቱ

ሰዎችን አንድ ነገር እንዲያደርጉ መምራት የሚገልጸው አንድ ነገር እንዲፈጸሙ ተጽዕኖ ማሳደርን ነው፡፡ "እስራኤል ኃጢአት እንዲያደርግ ተጽዕኖ በማሳደሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)