am_tn/1ki/15/25.md

2.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ቀሪው ምዕራፍ 15 እና 16 ስለ እስራኤል ነገሥታት ነው፡፡ እነዚህ ድርጊቶች የይሁዳ ንጉሥ አሳ በህይወት በነበረበት ወቅት የተፈጸሙ ናቸው፡፡

የይሁዳ ንጉሥ አሳ ሁለተኛ አመት

ይህ የሚያመለክተው የአሳን ዘመነመንግሥት ሁለተኛ አመት ነው፡፡ የዚህ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፤ "አሳ የይሁዳ ንጉሥ በነበረባቸው ለሁለት አመት ለተጠጉ ጊዜያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለሁለት አመታት በእስራኤል ላይ ነገሠ

"ናዳብ በእስራኤል ላይ ለሁለት አመታት ነገሠ"

በያህዌ እይታ ክፉ የሆነውን

የያህዌ እይታ የሚለው የሚወክለው የያህዌን ፍርድ ነው፡፡ "በያህዌ ፍርድ/ሚዛን ክፉ የሆነውን" ወይም "ያህዌ ክፉ ብሎ የሚቆጥረውን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአባቱ መንገድ ሄደ

እዚህ ስፍራ መሄድ የሚወክለው ድርጊትን ነው፡፡ "አባቱ ያደረገውን ተመሳሳይ ነገር አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በገዛ ራሱ ኃጢአት

በራሱ ኃጢአት መራመድ የሚለው የሚገልጸው አባቱ ካደረገው በተለየ መንገድ ኃጢአት መስራቱን ነው፡፡ "በራሱ መንገድ ኃጢአት አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህም እስራኤልን ወደ ኃጢአት መራ

ሰዎች አንድ ነገር እንዲያደርጉ መምራት የሚገልጸው ያንን ነገር እንዲያደርጉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደርን ነው፡፡ "ኃጢአት በመስራት እስራኤልም እንዲበድል ተጽዕኖ አሳደረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)