am_tn/1ki/15/23.md

2.1 KiB

የይሁዳ ነገሥታት ስራዎች በተጻፈበት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ አይደለምን?

ይህ ጥያቄ የዋለው አንባቢያን ስለ አብያ ያለው መረጃ በዚነህ ሌሎች መጽሐፍት ውስጥ እንደሚገኝ ለማሳወቅ ወይም ለማስታወስ ነው፡፡ ይህ በ1ነገሥት 14፡29 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ ቃለ ምልልሳዊው ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እነዚህ ታሪኮች የይሁዳ ነገሥታት የፈጸሟቸው ድርጊቶች በተጻፉባቸው መጽሐፍት ውስጥ ተጽፈዋል፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የይሁዳ ነገሥታት ስራዎች በተጻፈበት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ አይደለምን?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው ይህንን የይሁዳ ነገሥታት ድርጊቶች በተጻፈበት መጽሐፍ ጽፎታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አሳ ከአባቶቹ ጋር ተኛ

እዚህ ስፍራ መተኛት ሞትን የሚወክል ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ "አብያ እንደ አባቶቹ ሁሉ ሞተ" ወይም "እንደ አባቶቹ ሁሉ አብያ ሞተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚሉትን ይመልከቱ)

ከእነርሱ ጋር ተቀበረ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አባቱ ዳዊት

እዚህ ስፍራ "አባት" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የጥንት አባቶችን ነው፡፡