am_tn/1ki/15/01.md

2.6 KiB

በናባጥ ልጅ በንጉሥ ኢዮርብዓም አስራ ስምንተኛ አመት

ይህ የሚያመለክተው የኢዮርብዓምን ንግሥና አስራ ስምንተኛ አመት ነው፡፡ "ኢዮርብዓም ለ አስራ ስምንት አመታተት ያህል የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ በኋላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በአስራ ስምንተኛው አመት

"በ18ተኛው አመት" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉንም አይነት ኃጢአቶች አደረገ/ በኃጢአት መንገድ ተራመደ

ማድረግ/መራመድ የሚወክለው በኃጢአት መኖርን ነው፣ እናም በኃጢአት መራመድ የሚለው እነዚያን ኃጢአቶች መፈጸምን ነው፡፡ "አብያ እነዚይን ኃጢአቶች ማድረጉን ቀጠለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ዘመን በፊት አባቱ ያደርግ የነበረውን

እነዚህ ቁጥሮች በርካታ ነገሥታትን የሚያመለክቱ እንደመሆናቸው፣ የአብያን አባት ስም ማካተቱ ሊጠቅም ይችላል፡፡ ይህ መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "አባቱ ሮብዓም፣ ከአብያ ዘመን አስቀድሞ እንዳደረገው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ዘመን

ይህ ሀረግ የሚወክለው እርሱ ንጉሥ የነበረበትን ጊዜ ነው፡፡ የዚህ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "አብያ ንጉሥ ከነበረበት ጊዜ አስቀድሞ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ

ልቡ እንደ ዳዊት ልብ…አልተሰጠም ነበር

ልብ የሚወክለው መላ ስብዕናን ነው፡፡ "እንደ ዳዊት… አብያ ልቡን የሰጠ ሰው አልነበረም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)