am_tn/1ki/12/22.md

1.6 KiB

የእግዚአብሔር ቃል ……..እንዲህ ይላል፡፡

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ሲሆን እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ለማስተዋወቅ ያገለግላል፡፡ ተርጓሚ “እግዚአብሔር ይህን መልዕክት ተናገረ …እንዲህም አለ” ወይም “እግዚአብሔር እነዚህ ቃላት ተናገረ ..እንዲህም አለ”

ሳመያ

ይህ የሰው(ወንድ) ስም ነው፡፡

የእግዚአብሔር ሰው

የእግዚአብሔር ሰው የሚለው ሐረግ ለእግዚአብሔር ነብይ የአክብሮት መጥሪያ ስም ነው፡፡ ተርጓሚ “የእግዚአብሔር የሆነ ሰው፡፡ ወይም “የእግዚአብሔር ነብይ”

ለይሁዳና ለብንያም ቤት ሁሉ

እነዚህ “ቤት” ነገድን ወይም የዘር ሐረግን የመግለጫ ዘይቤ ነው፡፡ ተርጓሚ “ከይሁዳና ከብንያም ነገድ የሆኑ ህዝቦች ሁሉ

የእስራኤልንም ልጆች ወንድሞቻችሁን

“ወንድሞቻችሁን” ና የእስራኤል ልጆች የሚሉት ቃላት የተጣበቁና የሰሜኑ አስር ነገዶች የሚገልፅ ሲሆን በእነርሱ፤ በይሁዳና በብንያም መካከል ያለውን ቤተሰባዊ ግንኙነት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡

ይህ ነገር ከእኔ ዘንድ ነውና

ይህ በገቢር መልኩ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ተርጓሚ “ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ አደረኩ”