am_tn/1ch/26/26.md

1.6 KiB

ተሾመው ነበር

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አት: “ሀላፊነት ነበራቸው” (ፈሊጥ: ይመልከቱ)

ሻለቆችና የመቶ አለቆች

አማራጭ ትርጉሞች 1) እነዚህ ቁጥሮች አዛዦቹ ይመሯቸው የነበሩትን ወታደሮች ትክክለኛ ቁጥር ያሳያል፡፡ አት: “በ1,000 ወታደሮች ላይ አለቆች እና በ100 ወታደሮች ላይ አለቆች” ወይም 2) “ሺዎች” እና “መቶዎች” የሚሉት ቃላት ትክክለኛ ቁጥሮችን የሚያሳዩ ሳይሆን ነገር ግን የትልቅ እና የትንሽ የሰራዊት ክፍሎች ስሞች ናቸው፡፡ አት: “በትልቅ የሰራዊት ክፍል ላይ አዛዦች እና በትንሽ የሰራዊት ክፍሎች ላይ አዛዦች” (ቁጥሮች: ይመልከቱ)

ምርኮ

ሰራዊት ከድል በኃላ ከጠላቶቹ የሚወስደው

ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ … የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት

ይህ በገባሪ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: “ነብዩ ሳሙኤል … የጹሩያ ልጅ ኢዩአብ ለያህዌ እንደለዩት” (ገባሪ ወይም ተገባሪ: ይመልከቱ)

ቂስ … ኔር … ጽሩያ

እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ: ይመልከቱ)

የቀደሱት … ሁሉ

ይህ በገባሪ ቅርፅ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት: “መሪዎቹ የለዩት ሁሉ” (ገባሪ ወይም ተገባሪ: ይመልከቱ)