am_tn/1ch/21/01.md

2.7 KiB

በእስራኤል ላይ አንድ ጠላት ተነሳ

“ባላጋራ” ለሚለው ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞችን 1) ይህ የሚያመለክተው ለእስራኤል ችግር ለማምጣት የወሰነውን ሰይጣንን ነው ወይም 2) ይህ እስራኤልን ማስፈራራት የጀመረው የጠላት ጦር ነው ፡፡

ዳዊት እስራኤልን እንዲቆጥር አነሳሳው

ዳዊትን አሳተው፣ ቋንቋዎ አንድን ሰው በማስቆጣት ስህተት እንደሆነ የሚያውቀውን ነገር እንዲያደርግ በማድረግ ማሳሳትን የሚገልጽ ነገር ካለ ፣ እዚህ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ቁጥራቸውንም እንዳውቅ የእስራኤልን ሕዝብ ቁጠሩ

ከ 1ኛ ዜና 21፡ 5 በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ዳዊት ውጊያ የሚችሉትን ሰዎች ለመቁጠር ፈልጎ ነበር ፡፡

ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ

እስራኤላውያን እነዚህን ሁለት ከተሞች እንደ ብዙ ደቡባዊ እና ሰሜናዊ ከተሞች አድርገው ይመለከቱ ነበር። ዳዊት እነዚህን ከተሞች እስራኤልን በሙሉ ለማመልከት ይጠቀምባቸዋል ፡፡ (ሜሪዝምን : ይመልከቱ)

መቶ እጥፍ ይበልጣል

ኢዮአብ ሠራዊቱ መቶ እጥፍ እንዲሆንለት እናየበለጠ ኃያል እንዲሆኑ እንደሚመኝ በመናገር ገለጸ፡፡ (ግነት እና ማጠቃለል ፡ ይመልከቱ)

ግን ጌታዬ ንጉሡ ፣ ሁሉም ጌታዬን አያገለግሉምን? ጌታዬ ይህን ለምን ይፈልጋል? በእስራኤል ላይ ለምን ጥፋትን ያመጣል?

ኢዮብ የሕዝብ ቆጠራው ሃሳብ መልካም እንዳልሆነ ለዳዊት ለመግለጽ እነዚህን ሦስት አወያይ ጥያቄዎችን ተጠቅሟል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሔርን ከመታመን ይልቅ በሠራዊቱ መጠን የሚታመን ይመስላል እናም እስራኤልን ኃጢአተኛ ያደረገ ይመስላል ፡፡ እነዚህ አወያይ ጥያቄዎች እንደ መግለጫዎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። ኣት: ግን ጌታዬ ፣ ቀድሞ ሁሉም ያገልግሉሃል ፡፡ ጌታዬ ይህን መጠየቅ የለበትም ፡፡ ወታደራዊ ኃይልዎን ብቻ በመተማመን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ጥፋት ያመጣሉ ፡፡” (አወያይ መጠይቅን ፡ይመልከቱ)

ጌታዬ ይህን ለምን ይፈልጋል?

“ይህ” የሚለው ቃል የዳዊትን የእስራኤልን ወንዶችን ለመቁጠር ያቀደውን ዕቅድ ያመለክታል ፡፡