2.0 KiB
2.0 KiB
አጠቃላይ መረጃ
በ 1ኛ ዜና 19 ፡15 ላይ ከኢዮአብ ሸሽተው የመጡ ሶርያውያን በሌሎች ሶርያውያን ተጠናክረው እስራኤልን እንደገና እንደወጉ ቁጥር 16-19 ይናገራል ፡፡
ሶርያውያንም አይተዋል
ሶርያውያኑ የተገነዘቡት እንዳዩት ይነገራል። አት: - “ሶርያውያን ተረድተው ነበር” (የባህሪ ስምን ፡ ይመልከቱ)
ለማጠናከሪያነት ተልኳል
“ተጨማሪ ወታደሮችን ጠይቀዋል”
ሾፋክ…አድርአዛር
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው ፡፡ ( ስሞችን እንዴት እንደሚተረጉሙ ፡ይመልከቱ)
ዳዊትም ይህ ሲነገረው
ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: የዳዊት መልእክተኞች ብዙ የሶርያ ሠራዊት እየመጣ መሆኑን በነገሩት ጊዜ ( ገቢራዊን ወይም ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ)
እርሱ ሰብስቦ ... አስተካከለ
ዳዊት እነዚህን ነገሮች ብቻውን አላደረገም። የእርሱም ሆነ የአገሬው ሰዎች ረድተውታል። ኣት: “ዳዊትና አገልጋዮቹ ተሰበሰቡ… ዳዊትና አገልጋዮቹም አደራጁ” (ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን፡ ይመልከቱ)
እስራኤል ሁሉ
ይህ አጠቃላይ ነው ፡፡ የእስራኤል ህዝብ በሙሉ ወደ ውጊያው አልመጡም ፡፡ ኣት: - “እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው እስራኤላውያን” (ግነትን እና አጠቃላይን ፡ ይመልከቱ)
ዝግጅት አደረገ
“አደራጀ”
ተዋጉ
እዚህ “እርሱ” የሚለው ቃል ከዳዊት በተጨማሪ የዳዊትን ወታደሮች ያመለከታል ፡፡ ኣት: - “ሶርያውያን ዳዊትንና ወታደሮቹን ተዋጉ” ( ሁሉን በአንዱ መወከልን ፡ ይመልከቱ)