am_tn/1ch/17/22.md

1.5 KiB

አያያዥ መግለጫ

ዳዊት ያህዌን ማናገሩን ቀጠለ፡፡

አሁንም

እዚህ “አሁን” ማለት “በአሁኑ ጊዜ” አይደለም ፣ ነገር ግን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ነጥብ ትኩረትን ለማዞር ይጠቅማል፡፡

ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ለዘላለም የጸና ይሁን

፡ አት: - “ለእኔ እና ለቤቴ ቃል የገባኋውን አድርግ፣ እናም ቃል በጭራሽ አይለወጥ” (ገባሪ ወይም ተገባሪ፡ ይመልከቱ)

ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ

ዳዊት ስለ ራሱ በሦስተኛው መደብ መጠሪያ እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በመጀመሪያ መደብ መጠሪያ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: - “እኔ እና ቤተሰቤ” (የመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ ይመልከቱ)

ዘንድ ስምህ

እዚህ “ስም” የያህዌን ዝና ይወክላል። (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)

የባሪያህም የዳዊት ቤት

እዚህ “ቤት” ቤተሰብን ይወክላል፡፡ አት: - “ቤተሰቤ” (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)

በፊትህ ጸንቶአል

ይህ በገባሪ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: - “በአንተ ምክንያት የተጠበቀ” ወይም “ከአንተ የተነሳ ይቀጥላል” (ገባሪ ወይም ተገባሪ፡ ይመልከቱ)