am_tn/1ch/17/19.md

2.2 KiB

አያያዥ መግለጫ

ዳዊት ያህዌን መናገሩን ቀጠለ፡፡

ስለ ባሪያህ

እዚህ ላይ ዳዊት ራሱን “አገልጋይህ” ሲል ጠርቶታል፡፡ ይህ በመጀመሪያ መደብ መጠሪያ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: - “ለእኔ ጥቅም” ወይም “ለእኔ ጥቅሜ” (የመጀመሪያ ፣ ሁለተኛ ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ ይመልከቱ)

እንደ ልብህም አድርገሃል

“ያሰብከውን ለማሳካት”

እንዳንተ ያለ የለም፥ ከአንተ በቀር አምላክ የለም

እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው እና ለማጉላት የተደጋገሙ ናቸው፡፡ (ትይዩአዊ፡ ይመልከቱ)

በጆሮአችንም እንደሰማን ሁሉ

እዚህ “እኛ” የሚለው ቃል ዳዊትን እና የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል፡፡ (አግላይ እና አካታች “እኛ”: ይመልከቱ)

ለአንተም ሕዝብ … እንዳንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?

ይህ ጥያቄ እንደ እስራኤል ያለ ሌላ ሕዝብ እንደሌለ የሚያስተውል አሉታዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት: - “በምድር ላይ እንደዚህ ሕዝብ የለም … በታላቅ እና በሚያስደንቅ ሥራዎች” (መልስ የማይጠብቅ ጥያቄ: ይመልከቱ)

ግብጽ ካወጣኸው

ታሳቢ የሆነው መረጃ እነሱ ከባርነት እንደዳኑ ነው፡፡ አት: - “ከግብፅ ባርነት አዳናችሁ” (ታሳቢ የሆነ ዕውቀት እና ውስጠ ታዋቂ መረጃ፡ ይመልከቱ)

ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ

እዚህ “ስም” የያህዌን ስም ይወክላል። አት: - “ለሰዎች ሁሉ ማን እንደሆንክ ለማሳወቅ” (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)

አሕዛብን በማሳደድ

እዚህ “ሕዝቦች” በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦችን ይወክላል ፡፡ (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)