am_tn/1ch/17/09.md

2.4 KiB

አያያዥ መግለጫ

እግዚአብሄር ለንጉሥ ዳዊት የገባውን ቃል በነቢዩ ናታን በኩል መግለጹን ቀጠለ።

አጠቃላይ መረጃ:

በእነዚህ ቁጥሮች ላይ “የአንተ” እና “አንተ” የሚሉት ቃላት ዳዊትን ያመለክታሉ ፡፡

ስፍራ አደርግለታለሁ

“ቦታ እመርጣለሁ”

እተክለውማለሁ

እግዚአብሔር ህዝቡን በምድሪቱ ላይ በቋሚነት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲኖሩ በማድረግ በምድሪቱ ላይ እንደሚተክላቸው ያህል ተገልጻል፡፡ አት: - “እዚያ አስቀምጣቸዋለሁ” (ሜታፈር: ይመልከቱ)

ከዚያም በኋላ አይናወጥም

ይህ ገባሪ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: - “ማንም በጭራሽ አያስጨንቃቸውም” (ገባሪ ወይም ተገባሪ፡ ይመልከቱ)

እንደቀድሞው ዘመንና

እዚህ “ቀናት” ረዘም ያለ ጊዜን ይወክላል፡፡ አት: - “ከጊዜው”(የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)

ፈራጆች እንዳስነሣሁበት

የእስራኤል ሰዎች ወደ ከነዓን ምድር ከገቡ እና በኋላ ሚመሯቸው ነገሥታት ከመኖራቸው በፊት ፣ እግዚአብሔር በችግር ጊዜ እንዲመሯቸው “ፈራጆች” የተባሉ መሪዎችን ሾመ፡፡

በሕዝቤ በእስራኤል ላይ እንዲሆን

በሥልጣን መሆን ማለት በአንድ ሰው ላይ የበላይ መሆን ተብሎ ይጠራል፡፡ አት: - “ሕዝቤን እስራኤልን ይገዛል” (ፈሊጥ ይመልከቱ)

አያስጨንቁትም

አንድን ሰው ወይም እንስሳ ማጥቃት የማይችል ማድረግ

ቤት እንዲሠራልህ

እዚህ ላይ “ቤት” የሚለው አገላለጽ የሚያመለክተው የዳዊት ዘሮች እንደ እስራኤል ገዢዎች ሆነው መቀጠላቸውን ነው፡፡ በ 1ኛ ዜና 17፡4 ውስጥ እግዚአብሔር ለዳዊት ለያህዌ ቤት የሚሠራው እርሱ እንዳልሆነ ነገረው፡፡ እዚያም “ቤት” ቤተ መቅደስን ይወክላል፡፡ ቋንቋዎ ሁለቱንም ሀሳቦች መግለፅ የሚችል ቃል ካለው እዚህ እና በ17፡4 ውስጥ ይጠቀሙበት፡፡ (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)