am_tn/1ch/17/03.md

3.9 KiB

የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ እንዲህም አለው

“የእግዚአብሄር ቃል መጣለት” የሚለው ፈሊጥ ከእግዚአብሄር ልዩ መልዕክት መምጣቱን ለማሳየት የሚረዳ ነው፡፡ አት: “እግዚአብሄር ለናታን መልዕክት ሰጠው፡፡ ’ሂድ” ወይም “እግዚአብሄር ይህን መልዕክት ለናታን ተናገረው: ’ሂድ” አለ (ፈሊጥ ፡ይመልከቱ)

ሂድ፥ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ … የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም

ይህ ከጥቅሶቹ ውስጥ ጥቅሶች አሉት ፡፡ እነሱን በተዘዋዋሪ ጥቅሶች ለመተርጎም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ፡፡ አት: - “ሂድ ፣ እኔ የምኖርበትን ቤት የሚገነባው እርሱ እንደማይሆን ለአገልጋይዬ ለዳዊት ንገረው” (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ጥቅስ: ይመልከቱ)

ቤት መስራት

እዚህ “ቤት” ማለት መቅደስ ማለት ነው ፡፡ በ 1 ዜና 17፡10 ላይ ያህዌ ለዳዊት ቤት ይሠራል ይላል፡፡ እዚያ “ቤት” ማለት ቤተሰብ ማለት ነው፡፡ ቋንቋዎ ሁለቱንም ሀሳቦች መግለፅ የሚችል ቃል ካለው እዚህ እና በ 17፡10 ውስጥ ይጠቀሙበት፡፡

እስራኤልን ካወጣሁበት

ታሳቢ የሆነው መረጃ የሚያመለክተው እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ ምድር እንዳወጣ ነው፡፡ አት: - “እስራኤልን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከግብፅ ምድር አመጣሁ” (ታሳቢ የተደረገ እውቀት እና ውስጠ ታዋቂ መረጃን ይመልከቱ)

ድንኳን, ማደሪያ

“ድንኳን” እና “ማደሪያው ድንኳን” የሚሉት ቃላት አንድ ነገር የሚያመለክቱ ሲሆን ዘላቂ የሆነ ሕንፃ ባልነበረበት ስፍራ እንደኖረ ያጎላሉ፡፡ (ድግግሞሽ: ይመልከቱ)

ስለ ምን ቤትን ከዝግባ እንጨት አልሠራችሁልኝም? ብዬ ሕዝቤን ይጠብቅ ዘንድ ከእስራኤል ፈራጆች ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን?

ይህ በጥቅሱ ውስጥ ጥቅስ አለው፡፡ ቀጥተኛው ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት: “የዝግባ ቤት ለምን አልሰራችሁልኝም ብዬ ለሕዝቤ እረኛ እንዲሆኑ ከሾምኳችው የእስራኤል መሪዎችን ጠይቄያለሁን?” (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ጥቅስ: ይመልከቱ)

ከእስራኤል ፈራጆች ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን?

ያህዌ ማንንም የእስራኤል መሪዎች ቤት እንዲሠሩለት በጭራሽ እንዳልጠየቃቸው ለማጉላት ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት: - “ማንንም የእስራኤል መሪዎች አንዳች ነገር በጭራሽ አላልኩም” (መልስ የማይጠብቅ ጥያቄ: ይመልከቱ)

ሕዝቤን ይጠብቅ ዘንድ

የእስራኤል ሕዝብ መሪዎች እንደ እረኞች ፣ ህዝቡም በግ እንደሆኑ ተደርጎ ተገልፃል፡፡ (ዘይቤ: ይመልከቱ)

ስለ ምን ቤትን ከዝግባ እንጨት አልሠራችሁልኝም?

ይህዌ ይህን ጥያቄ መሪዎችን ጠይቆ ቢሆን፣ ጥያቄው የዝግባ ቤት ስላልሰሩለት መተንኮሻ ነበር፡፡ ነገር ግን ፣ ያህዌ ከዚህ ቀደም ይህን ጥያቄ እንዳልጠየቃቸው ተናግሯል፡፡ አት: - “የዝግባ ቤት ልትሠሩልኝ ይገባ ነበር።” (መልስ የማይጠብቅ ጥያቄ: ይመልከቱ)