am_tn/1ch/17/01.md

1.9 KiB

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ የታሪኩን አዲስ ክፍል ጅምር ለመጠቆም እዚህ የሚያገለገል ነው፡፡ ቋንቋዎ ይህንን የሚያደርግበት መንገድ ካለው እዚህ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ (የአዲስ ክስተት መግቢያ፡ ይመልከቱ)

በተቀመጠ ጊዜ

የመንቀሳቀስ ወይም የመቀየር ፍላጎት ሳይኖር ምቾት እና ደስተኛ

እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ

ዝግባ በጥንካሬው የሚታወቅ ዓይነት ዛፍ ነው፡፡ በባህልዎ ውስጥ ተመጣጣኝ የሆነ የዛፍ አይነት ካለዎት ያንን ስም መጠቀም ይችላሉ፣ ካልሆነ ግን ይህን ስም እንደገና መጠቀም ይችላሉ፡፡ አት: - “እኔ ጠንካራ እና በቋሚ ቤት ውስጥ እኖራለሁ” (ታሳቢ እወቀት እና ውስጠ ታዋቁ መረጃ ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል

ድንኳኖች ጊዜያዊ መኖሪያ ናቸው፡፡ በባህልዎ ውስጥ ድንኳን ከሌለዎት ይህንን በተለየ ቃል መጥራት ይችላሉ፡፡ አት: - “የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ጊዜያዊ ቦታ ውስጥ ይቆያል” (ታሳቢ እወቀት እና ውስጠ ታዋቁ መረጃ ይመልከቱ)

በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ

እዚህ “ልብ” አእምሮን ይወክላል፡፡ አት: - “ማድረግ ያለብህን አድርግ” (የባሕሪ ስም: ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው

እዚህ “ካንተ ጋር” ማለት እግዚአብሔር ዳዊትን እየረዳ እና እየባረከው ነው ማለት ነው፡፡ (ፈሊጥ:ይመልከቱ)