am_tn/1ch/14/08.md

916 B

አሁን

ጸሐፊው ይህን ቃል በ1 ዜና 14:3-7 ያለውን የዳራ መረጃ መስጠት መጨረሱንና አዲሱን የታሪኩን ክፍል መጀመሩን ያሳያል፡፡ ቋንቋዎ ይህንን የሚያከናውንበት የተለየ መንገድ ሊኖረው ይችላል ፡፡

ዳዊት ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ

ይህ በገባሪ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አት: - “የእስራኤል ሽማግሌዎች ዳዊትን ንጉሥ አድርገው ቀቡት” (ገባሪ ወይም ተገባሪ፡ ይመልከቱ)

ሊጋጠማቸው ወጣ

ዳዊት ጦሩን እንዲዋጓቸው እንላከ ታሳቢ ያደርጋል፡፡ አት: “ጦሩን እንዲዋጓቸው ላካቸው” (ታሳቢ የሆነ እውቀት እና ውስጠ ታዋቂ መረጃ: ይመልከቱ)

በራፋይም ሸለቆ

ይህ የቦታ ስም ነው፡፡