am_tn/1ch/13/05.md

2.7 KiB

ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ

እዚህ ላይ “ሁሉም” የሚለው ቃል አጠቃላይ ነው፡፡ ሐረጉ ዳዊት ከመላው እስራኤል ሰዎችን ሰብስቧል ማለት እንጂ፣ በእስራኤል እያንዳንዱን ሰብስቧል ማለት አይደለም፡፡ አት: - “ዳዊት ከእስራኤል ሁሉ ሰዎችን ሰበሰበ” (ቃል አጋኖ እና ማጠቃለል: ይመልከቱ)

ሌቦ ሐማት… ቂርያትይዓሪም… በኣላ

እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው፡፡ “በኣላ” ለቂርያትይዓሪም ሌላ ስም ነው፡፡ (የስሞችን አተረጓጎም ፡ ይመልከቱ) እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው ፡፡ ‹በኣላ› ለቂርያትይዓሪም ሌላ ስም ነው ፡፡ (ስሞችን እንዴት እንደሚተረጎሙ ይመልከቱ)

በይሁዳ ወዳለችው

በይሁዳ ያለው

የእግዚአብሔርንም ታቦት ያመጡ ዘንድ

ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚወስዱት ያመለክታል፡፡ AT: “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ” (ታሳቢ የተደረገ እውቀት እና ውስጠ ታዋቁ መረጃ: ይመልከቱ)

ያመጡ ዘንድ

ኢየሩሳሌምን በእስራኤል ከሚገኙ ከማንኛውም ስፍራ ከፍ ያለ ነው ፣ ስለሆነም እስራኤላውያን ወደ ኢየሩሳሌም ማወጣት እና ከእርሷ መውረድ በማለት መናገራቸው የተለመደ ነገር ነበር ፡፡

በያህዌ ስም የሚጠራ

ይህ በቀጥተኛ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “በስም የተጠሩ” የሚለው ፈሊጥ የሚያመለክተው የነገሩ ባለቤት የሆነውን ነው። አት: - “የእግዚአብሔር የሆነው” ወይም 2) ታቦቱ የእግዚአብሔር ስም በላዩ ላይ አለ። አት: - “የያህዌን ስም የተሸከመ” (ፈሊጥን፡ ተመልከት)

በኪሩቤል ላይ የተቀመጠውን

ኪሩቤል ማለት በቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ ላይ ያሉት መሆናቸውን ግልፅ ማደረግ ያስፈልጋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የቃል ኪዳኑን ታቦት እንደ የእግዚአብሔር መቀመጫ ከላይ ሆኖ በሰማይ በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠበት እግረኛ ይመስሉት ነበር፡፡ አት: “በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ከኪሩቤል በላይ በዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው” (ታሳቢ የተደረገ እውቀት እና ውስጠ ታዋቁ መረጃ: ይመልከቱ)