am_tn/1ch/11/18.md

1.4 KiB

ሦስቱ ኃያላን

“3 ኃያላን ሰዎች”

የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ

'በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት መካከል በመዋጋት አለፉጉ'

በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውሃ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚያመለክቱት ተመሳሳይውን የውሃ ምንጭ ነው ፡፡ ሁለተኛው በቤተልሔም ውስጥ የትኛው የውሃ ምንጭ እንደሆነ ያሳያል ፡፡

ለእግዚአብሔር አፍስሶ

ይህ ማለት ውሃውን ለያህዌ መባ አድርጎ አፈሰሰ ማለት ነው፡፡

ይህን አደርግ ዘንድ … ይከልክለኝ

“እንደዚህ ያለ ነገር በጭራሽ አላደርግም!” ወይም “ይህን ፈጽሞ ማድረግ የለብኝም!”

በነፍሳቸው የደፈሩትም እነዚህ ሰዎች ደም እጠጣለሁን?

ሰዎቹ ውሃውን ወደ እርሱ ለማምጣት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ስለነበር ዳዊት ውሃውን እንደ ደም አድርጎ ተናገረው፡፡ ይህንን ለማጉላት ጥያቄን ይጠቀማል ፡፡ ይህ አጻጻፍ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት: - “ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ ሚጠጡ ይህ ውሃ መጠጣት የለብኝም።”