24 lines
2.0 KiB
Markdown
24 lines
2.0 KiB
Markdown
|
# መዋቅሩና አቀራረቡ
|
||
|
|
||
|
ይህ ምዕራፍ የተጻፈው እንደ ፍርድ ቤት ጉዳይ ወይም እግዚአብሔር በራሱ ሕዝብ ላይ ሙግት እንዳለው ሆኖ ነው።
|
||
|
|
||
|
# በሙግቱ ውስጥ ያሉት ስሞች በዚህ ምዕራፍ ለመተርጎም አስቸጋሪ ከሚሆኑት ውስጥ ናቸው
|
||
|
|
||
|
ሙሴ፣ አሮንና ማርያም በእስራኤል ላይ ለእግዚአብሔር ምስክር ሆነው ተጠቅሰዋል። አክዓብና ዖምሪ እግዚአብሔርን እንዳልተከተሉ ክፉ ነገሥታት ሆነው ተጠቅሰዋል። ለሙሴ ሕግ መታዘዝ ለሕጉ ካለመታዘዝ ጋር ተነጻጽሯል።
|
||
|
|
||
|
# እንግዲህ ስሙ … የእግዚአብሔርን ሙግት ስሙ
|
||
|
|
||
|
ሚክያስ ሊሰሙት ይችሉ ይመስል ለተራሮች ሲናገር የሚናገረው ለእስራኤል ሕዝብ ነው፤ ስለዚህ በሁለቱም አገላለጽ “ስሙ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው።
|
||
|
|
||
|
# ተነሥ … አቅርብ … ድምፅህ …
|
||
|
|
||
|
ሚክያስ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፤ ስለዚህ ትዕዛዞቹና “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው።
|
||
|
|
||
|
# ተነሥና በተራሮቹ ፊት ነገርህን አቅርብ፤ ኮረብቶቹም ድምፅህን ይስሙ
|
||
|
|
||
|
እግዚአብሔር በፍርድ ቤት እንዳለና ተራሮችና ኮረብቶች ፈራጆቹ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል። የእስራኤል ሕዝብ ያደረጉትን ለምን እንዳደረጉ ለዳኞቹ እንዲናገሩ ያዛቸዋል።
|
||
|
|
||
|
# ተራሮቹ … ኮረብቶቹ … የጸኑት የምድር መሠረቶች
|
||
|
|
||
|
ሚክያስ ሰዎች እንደሆኑ ቆጥሮ ለእነዚህ ነገሮች ይናገራል። ሚክያስ ተራሮችን፣ ኮረብቶችንና የምድርን መሠረቶች በሕዝቡ ጣዖት አምላኪነት ላይ ዘላለማዊ ምስክር አድርጎ ያቀርባቸዋል።
|