20 lines
2.6 KiB
Markdown
20 lines
2.6 KiB
Markdown
|
# ስለዚህ አሁን፣ የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?
|
||
|
|
||
|
እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ግብጽንና አሦርን አነርሱን እንዲረዱአቸው መጠየቃቸው ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንደማያመጣላቸው ለሕዝቡ ለማስታወስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ግብጽ በመሄድ ከሺሖር ወንዝ ውኃ መጠጣት ወይም ወደ አሦር በመሄድ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውኃ መጠጣት ለእናንተ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )
|
||
|
|
||
|
# የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?
|
||
|
|
||
|
እነዚህ የግብጽንና የአሦርን ሰራዊት እነርሱን እንዲረዱአቸው ለመጠየቃቸው ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግብጻውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ … አሦራውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ሺሖር
|
||
|
|
||
|
ይህ ከግብጽጋር የተያያዘ የአንድ ምንጭ ስም ነው፡፡ ምናልባት የአባይ ወንዝ ገባር ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች አባይ ብለው ይጠሩታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሺሖር ምንጭ” ወይም “የሺሖር ወንዝ” ወይም “የአባይ ወንዝ” (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ክፋትሽ ይገስጽሻል፣ ክህደትሽ ይቀጣሻል
|
||
|
|
||
|
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ቅጣታቸው የክፉ ስራቸው ውጤት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉና ከዳተኛ ስለሆንሽ እቀጣሻለሁ” (ሰውኛ ዘይቤ እና ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ክፉና መራራ ነው
|
||
|
|
||
|
እዚህ ላይ “መራራ” የሚለው ቃል “ክፉ” የሚለውን ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም መራራ የሆነ ክፋት ነው” ወይም “እጅግ በጣም ክፉ ነው” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
|