am_tn/isa/28/01.md

24 lines
1.7 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# በወይን ጠጅ በተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ … ወዮ ለትዕቢት አክሊል
"አክሊል' የሚለው ከአበባ የሚሠራን ዘውድ ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ከለምለም ሸለቆ በላይ የተቀመጠችውን የእስራኤልን ዋና ከተማ የሰማሪያ ከተማን ይወክላል፡፡ የአክሊል አበባዎች እንደሚያረጁና ውበታቸው እንደሚጠፋ የሰማሪያና የሕዝቧ መጥፋት ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# እነሆ
"ስሙ' ወይም "ልብ በሉ'
# በወይን ጠጅ ለተሸነፉ
"በወይን ጠጅ ለሰከሩ'
# ጌታ ኃያልና ብርቱ የሆነውን አንድ ሰው ይልካል
በዚህ ስፍራ አንድ ሰው የሚለው ኃያል ሠራዊቱን የሚወክለውን ኃያል ንጉሥ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ጌታ አንድን ንጉሥ ከኃያል ሠራዊቱ ጋር ይልከዋል' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
# የበረዶ ዝናብ
"የበረዶ ዝናብ' ወይም የበረዶ ወጨፎ ጠንካራ የበረዶ ክፋዮች ከሰማይ ሲወርዱ ይከሰታል፡፡ ይህ የሰማሪያን ሕዝብ ለማጥፋት እግዚአብሔር የሚልከውን የጠላት ጦር የሚያመለክት ዘይቤአዊ ንግግር ነው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
# እያንዳንዱን አክሊል ወደ መሬት ይጥለዋል
ንጉሡና ኃያል ሠራዊቱ የሰማሪያና ሕዝብና ከተማቸውን ማጥፋቱ የሕዝቡን አክሊል ምድር ላይ እንደመጣል ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)