20 lines
2.5 KiB
Markdown
20 lines
2.5 KiB
Markdown
|
# ጥፋትን እከምርባቸዋለሁ
|
||
|
|
||
|
በእስራኤላውያን አናት ላይ የሚቆልላቸው ቆሻሻዎች የሆኑ በሚመስል መልኩ በእስራኤላውያን ላይ ስለሚደርስባቸው መጥፎ ነገሮች እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ብዙ መጥፎ ነገሮች እንደሚደርሱባቸው አረጋግጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እወነጭፋቸዋለሁ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ጋ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ በእርግጠኝነት እንዲደርስባቸው የሚያደርጋቸውን መጥፎ ነገሮች አንድ ሰው በቀስቱ ፍላጻዎችን ከማስወንጨፉ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “እነርሱን ለመግደል ማድረግ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# በረሀብ ያልቃሉ
|
||
|
|
||
|
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። የነገር ስም የሆነው “ረሀብ” “ይራባሉ” ወደሚል ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይዝላሉ፣ በመራባቸው ምክንያትም ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# እነርሱ -- ረሀብ እና በሚያቃጥል ሙቀትና በአሰቃቂ ጥፋት ይዋጣሉ
|
||
|
|
||
|
“የሚያቃጥል እሳት” ለሚለው ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እስራኤላውያን በንዳድ ይሰቃያሉ ወይም 2) በድርቅ ወይም በረሀብ ወቅት የአየሩ ሁኔታ ባለተለመደ መልኩ ሞቃት ይሆናል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነርሱ . . . ረሀብ፣ የሚያቃጥል ሙቀትና አሰቃቂ ጥፋት ይውጣቸዋል” ወይም “እነርሱ . . . ረሀብ፣ በሚያቃጥል ሙቀትና በአሰቃቂ ጥፋት ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# የዱር አራዊትን ጥርስ፣ አፈር ላይ ከሚሳቡ ነገሮች መርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ
|
||
|
|
||
|
ጥርስና መርዝ እንስሳው እነዚህን ነገሮች በመጠቀም የሚገድልባቸው ናቸው። አ.ት፡ “እንዲነክሷቸው የዱር አራዊትን፣ ነክሰው እንዲመርዟቸው በአፈር ላይ የሚሳቡትን ነገሮች እልካለሁ” (See: Synecdoche)
|