am_tn/deu/15/15.md

28 lines
1.9 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ባሪያ እንደነበርህ አስብ
እዚህ ጋ “አንተ” የሚለው ቃል ለብዙ ዓመታትባሪያዎች የነበሩትን ቅድም አያቶቹን ይጨምራል። አ.ት፡ “በአንድ ወቅት የአንተም ሕዝብ ባሪያዎች እንደነበሩ አስብ” (See: Forms of You)
# አምላክህ እግዚአብሔር ተቤዥቶሃል
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ በግብፅ ባሪያ ከነበረበት ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ የከፈለ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# ‘ከአንተ አልለይም’ ቢልህ
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከአንተ አልለይም ቢልህ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ
# ቤትህ
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው የሰውየውን ቤተሰብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# ከዚያም ወስፌ ወስደህ በሩ ላይ አስደግፈህ ጆሮውን ትበሳዋለህ
“ከዚያም ራሱን በቤትህ የበር መቃን ላይ ታስደግፍና በጆሮው የጉትቻ ማንጠልጠያ ቦታ ላይ የወስፌው ጫፍ እንጨቱ ጋ እስኪደርስ ትበሳዋለህ”
# ወስፌ
ቀዳዳ ለማበጀት የሚጠቅም ጫፉ የሾለና ቀጥ ያለ መሣሪያ (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
# ዕድሜ ልኩን
“እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ” ወይም “እስኪሞት ድረስ”