24 lines
2.1 KiB
Markdown
24 lines
2.1 KiB
Markdown
|
# ኢታይ
|
||
|
|
||
|
ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ጌትያዊ
|
||
|
|
||
|
ይህን የህዝብ ወገን ስም በ2 ሳሙኤል 6፡10 ላይ እንደ ተረጎሙት በተመሳሳይ ይተርጉሙ፡፡
|
||
|
|
||
|
# ለምን ከእኛ ጋር ትመጣለህ?
|
||
|
|
||
|
ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚያመለክተው ንጉሡ እነርሱ ከእርሱ ጋር መሄድ አለባቸው ብሎ አንደማያስብ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ ከእኛ ጋር መሄድ አያስፈልግህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ለምን አንተ ከእኛ ጋር እንድትንከራተት አደርጋለሁ?
|
||
|
|
||
|
ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ዳዊት ኢታይ እንዲመጣ አለመፈለጉን ያጎላል፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ከእኛ ጋር እንድትዞር ላደርግ አልፈልግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የመጣኸው ገና ትናንትን ነው
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "ትናንት" የሚለው በቅርብ ጊዜ የሚለውን ለማጋነን ነው፡፡ የጌት ሰው ኢታይ በዚያ ብዙ አመት ኖሯል፡፡ "በዚህ ስፍራ የኖርከው ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደመሆኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ታማኝነት እና እውነተኝነት ከአንተ ጋር ይሁኑ
|
||
|
|
||
|
ይህ ዳዊት ለእርሱ የሰጠው በረከት/ምርቃት ነው፡፡ "ያህዌ ሁሌም ለአንተ ታማኝነቱን እና እውነቱን ያድርግልህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
|