am_tn/job/38/39.md

40 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አያያዥ ሀሳብ፡
ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል
# አጠቃላይ መረጃ፡
ያህዌ ኢዮብን ይህን ጥያቄ የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ አንበሶችን እንዴት እንደሚመግብ አለማወቁን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)
# አንተ አድብተህ ጠብቀህ… ማደን ትችላለህ?
ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አድብተህ ጠብቀህ…ማደን ትችል እንደሆን ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)
# የሚታደን
"ታዳኝ፡፡" ይህ አንድ አንበሳ አድኖ የሚበላው እንስሳ ነው፡፡
# ሴት አንበሳ
ይህች ሴት አንበሳ ናት
# የምግብ ፍላጎት
ረሃብ
# የእርሷ የአንበሳ ግልገል
"የአንበሳ ግልግል/ደቦል" ለራሳቸው አድነው መመገብ የጀመሩ ደቦል አንበሶች
# ዋሻ
"ዋሻ" አንበሳ የሚጠለልበት መኖሪያ/የአውሬ ዋሻ/ ነው
# በሚደበቅበት ጊዜ የሚጠለልበት
"በቁጥቋጦ ውስጥ መደበቅ፡፡" አንበሶች ሲያድኑ ጥቅጥቅ ባለ ሳር ቅጠል ውስጥ ይደበቃሉ
# አድብቶ መጠበቅ
በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው መረጃ አንበሶች ተደብቀው የሚያድኑት እንስሳ እስኪቀርብ ይጠብቃሉ፡፡ "ታዳኙን ተጋድሞ/አድፍጦ መጠበቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)