25ከዚያም ሌሎች ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይመልሱላቸዋል፣ ‘ይህ የደረሰባቸው ከግብጽ ካወጣቸው ከአምላካቸው ከያህዌ ጋር የገቡትን ኪዳን ለመታዘዝ ስላልወደዱ ነው፡፡ 26ይልቁንም፣ ከዚያ አስቀድመው የማያመልኳቸውን ሌሎች አማልዕክት አመለኩ፣ ያህዌ እንዲያመልኳቸው ያልነገራቸውን አማልዕክትን አመለኩ፡፡